top of page
Search

በቅድስት ቤተክርስትያናች በየእለቱ የሚከበሩ በአላት!

  • Writer: ጎዶልያስ
    ጎዶልያስ
  • Jun 7, 2019
  • 3 min read

Updated: Jun 17, 2019

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ለዛሬ በቅድስት ቤተክርስትያናችን በየእለቱ የሚከበሩ በአላት ይዘንላቹ ቀርበናል ከ 1--30 ያሉት በአላት

በ1----- ልደታ ማርያም፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ጻድቁ ኢዮብ፣ ነቢዩ ኤልያስ፣ሐዋርያው በርተሎሜዎስ፣ ቅድስት ሶስና፣ አባ ሚልኪ፣ ቅዱስ መክሲሞስ

በ2.....ሐዋርያው ታዴዎስ፣ ሠለስቱ ምዕት፣ ቅድስት አትናስያ፣ አቡነ እንድርያኖስ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ፣ አባ ጉባ

በ3......ባዕታ ማርያም፣ ቅዱስ ፋኑኤል፣ አባ ዜና ማርቆስ፣ አባ ሊባኖስ፣ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ . በ4.....ወልደ ነጎድጓድ፣ ሐዋርያው እንድርያስ፣ ጻድቁ መልከ ጼዴቅ፣አባ መቃርዮስ፣ ሰማዕቱ ፊቁጦር፣ አብርሃም ወአጽብሐዮ

በ5......ጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ አሮን፣ አቡነ ዮሐኒ፣ አቡነ አሞኒ፣ አቡነ መልአክ ክርስቶስሐንስ

በ6......ግዝረተ ኢየሱስ፣ ቁስቋም ማርያም፣ ነቢዩ ኢያሱ፣ ቅድስት አርሴማ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ፣ አቡነ ተጠምቀ መድኅን

በ7......አጋዝዕተ ዓለም ሥላሴ፣ ስዕለተ ማርያም፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ቅድስት እኅተ ጴጥሮስ . በ8......አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል)፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴ፣ ሐዋርያው ማትያስ፣ ካህኑ ዘካርያስ፣ አባ ኪሮስ፣ ቅድስት አመተ ክርስቶስ . በ9.......ሐዋርያው ቶማስ፣ ቅዱስ አትናትዮስ፣ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ አቡነ ብጹዕ አምላክ፣ አቡነ ህልያና፣ አቡነ ፂዋ ወንጌል . በ10.....መስቀለ ኢየሱስ፣ ሐዋርያው ናትናኤል፣ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፣ ጼዴንያ ማርያም፣ ሰማዕቱ ሠርጊስ

በ11.....ሐና ማርያም፣ ቅዱስ ኢያቄም፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ሰማዕቱ ፋሲለደስ፣ አቡነ ሐራ ድንግል፣ አባ አሌፍ፣ ቅድስት ታኦድራ፣ ቅዱስ ገላውዴዎስ

በ12......ቅዱስ ሚካኤል፣ ሐዋርያው ማቴዎስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ አባ ሳሙኤል፣ ቅድስት አፎሚያ፣ ቅዱስ ዲሜጥሮስ . በ13.....እግዚአብሔር አብ፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ እልፍ አእላፍ መላእክት፣ አቡነ ዘርዐ ብሩክ፣ አቡነ ተንሳኢ ክርስቶስ. .. በ14......አቡነ አረጋዊ፣ አባ ጳኩሚስ፣ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፣ አቡነ ተስፋ ጽዮን፣ ሰማዕቱ አብሮኮሮስ፣ አባ ዘሚካኤል፣ ሙሴ ጸሊም . በ15.....ቅዱስ ቂርቆስ፣ አቡነ ቆራይ፣ ቅድስት ለባሲተ ክርስቶስ፣አቡነ ያሳይ፣ አቡነ ተስፋ ሐዋርያ፣ አባ ሚናት . በ16......ኪዳነምሕረት፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ፣ ቅድስት እየሉጣ፣ ሰማዕቱ ጊጋር፣ አባ ጽሕማ፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ አባ ጳውሊ . በ17......ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ፣ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ አቡነ ገሪማ፣ ቅዱስ ሚናስ፣ ጽላተ ሙሴ

በ18......ሐዋርያው ፊልጶስ፣ አቡነ ዮስጣጤዎስ፣ ቅዱስ ማርያዕቆብ፣ሰማዕቱ ሮማኖስ፣ ሊቁ ቅዱስ አባ ዳንኤል፣ አቡነ አኖርዮስ፣ ማዕቀበ አልፋ . በ19......ቅዱስ ገብርኤል፣ ሠለስቱ ደቂቅ፣ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ፣ቅዱስ ሐርቤ (ገ/ማርያም)፣ አብየ እግዚእ፣ አቡነ ጸጋ ኢየሱስ፣ አቡነ እናዝጊ . በ20.....ነቢዩ ኤልሳዕ፣ ሕንጸታ ቤተክርስቲያን፣ ቅዱስ ዮሐንስ አንፂር፣ ቅድስት ወለተ ሰማዕት . በ21......እመቤታችን ድንግል ማርያም፣ ነቢዩ ኢዩኤል፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ ቅድስት ሔራኒ፣ ጻድቁ ቆጵርያኖስ . በ22.......ቅዱስ ዑራኤል፣ ወንጌላዊው ሉቃስ፣ አባ ደቅስዮስ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ሰማዕቱ ቶኮሎስ፣ ሰማዕቱ ቅዱስ ማሩና . በ23.......ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ልበ አምላክ ዳዊት፣ ጠቢቡ ሰለሞን፣ሰማዕቱ ቅዱስ ቤድራቶስ

በ24......24ቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፣ ቅድስት አስቴር እስራኤላዊት፣ አባ ሙሴ ጸሊም፣ አቡነ መርቆርዮስ፣ አባ ኖብ፣ ቅድስት ወለተ ሙሴ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብጽ

በ25......ነቢዩ ዮናስ፣ ሰማዕቱ መርቆርዮስ፣ አቡነ አቢብ፣ ሕጻን ሰሎሜ፣ አባ ሕጻን ሞዐ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ከማ . በ26......ነቢዩ ሆሴዕ፣ አረጋዊ ዮሴፍ፣ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፣ ቶማስ ዘህንደኬ፣ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ)፣ አቡነ ሐብተ ማርያም፣ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ፣ አቡነ ሰበነ ድንግል . በ27.....መድኃኒዓለም፣ ርዕሰ አበው ሔኖክ፣ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ፣ ቅዱስ ያዕቆብ ዘአርማንያ፣ አባ ጽጌ ድንግል፣ አቡነ መብዐ ጽዮን (ተክለ ማርያም)፣ አቡነ ተክለ አዶናይ፣ አቡነ ተክለ ሐዋርያ . በ28.....አማኑኤል፣ አብርሐም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ አባ ይምአታ፣ አባ ሊቃኖስ፣ ቅድስት አመተ ክርስቶስ፣ አመተ ጊዮርጊስ . በ29......ባዕለ ወልድ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ አቡነ መዝርዐተ ክርስቶስ፣ አባ አፍጼ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ . በ30......መጥምቁ ዮሐንስ፣ ወንጌላዊው ማርቆስ፣ ቅድስት ማርያም ክብራ፣ አቡነ አሮን ዘገሊላ

የቅዱሳን በረከት አይለየን::

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አያናውጧትም ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም!

ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)

ለሌሎች እንዲዳረስ SHARE እና LIKE እንዲያደርጉ በሚጠፉትና በሚድኑት መሀል የክርስቶስ መአዛ በሆኑት በቅዱሳን ስም እንጠይቃለን!

ቤተክርስቲያን.... መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን። ተጨማሪ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎችን እና መዝሙሮችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ፌስቡክ https://www.facebook.com/godolyass ቴሌግራም https://t.me/rohobotorthodox ዌብሳይት https://godolyas.wixsite.com/godolyas ዩትዩብ https://www.youtube.com/channel/UCNzT-PH-N1idwo1UTqsVaiw


 
 
 

Recent Posts

See All
የሰኔ ጾም

ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ ይልቁንም በብሉይ...

 
 
 

Commentaires


Post: Blog2_Post

©2019 by ጎዶልያስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር. Proudly created with Wix.com

bottom of page